NMHDO crucial role in Women Empowerment By assisting Beyena Association in Aksum Published on Tigray Women’s Affairs Bureau June 2016: Volume 13 AREYA magazine pages 12 and 13(Amharic))

ለሴቶች ብይን የሰጠች ማህበር
ትግራይ የሴቶች ጉዳይ ቢሮ ሰኔ 2008 ቁጥር 13 ዕርያ መፅሔት ገፅ 12ና 13 የታተመ.
“በየና” የሚል ስም የተጎናፀፈችው ከቀድሞ አባሎቿ ሲሆን ትርጉሙ ደግሞ ዛሬ ለመቆጠባችን በኑራችን ላይ የተሻለ ለውጥ ለማምጣት ለነገ ሕይወታችን  ላይ ብይን መስጠት እንችላለን  ይላሉ የማህበራቱ አባላት ህልማቸውን ጋህድ አድርገዋል።

በየና ብድር እና ቁጠባ ህብረት ስራ ማህበር ጥቅምት 12/2003 ዓ.ም ለ50 ሴቶች  ህጋዊ ተቋም ተብላ የተቋቋመች ሲሆን  በአሁን ሰዓት በአክሱም ከተማ  ከሚገኙ አራት ቀበሌዎች ማለትም ማዕከል ሐውልት ኃየሎም እና ክንደራ 585 ሴቶችን አቅፋ ለለውጥ ላይ  እየገሰገሰች የምትገኝ ማህበር ነች።

በየና አጋሮቿ ከመደራጀታቸው በፊት ምንም አይነት  የገቢ ምንጭ ሆነ ለማህበራቸው ብድር ሊያመቻችላቸው የሚችል ተቋም ባለመኖሩና ሰለ ብድርና ቁጠባ ግንዛቤ ስላልነበራቸው እንደ ትልቅ  እንቅፋት ሆኖባቸው ነበር። ይህን ችግራቸው የተገነዘበ ኒው ሚሊንየም ሆፕ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ስለ ተደራጅተው  መስራትና ብድርና ቁጠባ ክህሎታቸው እንዲጨምር ተደጋጋሚ ስልጠናዎችን በአክሱም ደረጃ ለተለያዩ ሴቶች በመስጠቱና ማህበር በየናም የዚህ አካሄድ ተጠቃሚ መሆኗ የተሻለ አደረጃጀት እንድትይዝ አስችሏታል።

ከዛም በመቀጠል ማህበሯ ስራዎችዋን ለመፈፀም  ከአባሎቿ  5 አመራር በመምረጥ ፣  በ3 ቁጥር ኮሚቴን  6 ብድርና ቁጠባ ኮሚቴ በመምረጥ የስራውን ድርሻ  ደግሞ በሊቀመምበር ም/ሊቀመንበር እና ሒሳብ ሰራተኛ  እንዲሰራ አድርጓል።

የብድርና ቁጠባው አመራሮች ማህበሮች ማህበሩን ወደ ተሻለ የአሰራር ስልት ለመውሰድ የተለያዩ ሰነዶችን በማዘጋጀት ብሎም  በጠቅላላ ጉባኤ እያፀደቁ መተዳደሪያ  ደንብ የወጪና የገቢ  መዛግብትና የሰራተኛ አስተዳደር መመሪያዎችን በመንደፍ ስልጠናዎችን በመስጠት ወደ ተሻለ ማህበር እንዲሸጋገሩ ለማድረግ ተችለዋል።

በየና ብድር እና ቁጠባ  ህብረት ሥራ ማህበር ስራ ስትጀምር የነበራት የገንዘብ አቅም  መነሻው  በኒው  ሚሊንየም ሆፕ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን ለአባላቶቿ ለእያንዳዳቸው 2,000 በብድር መልክ በመስጠት ጠቅላላ 100 ሺህ የጀመረች ሲሆን  ባሁን ሰዓት በ 2000 የተጀመረ ብድር አሁን ላይ እስከ 100,000 ብር ድረስ ማበደር ችሏል ጠቅላላ  ካፒታሏ ደግሞ 108,162 ሺህ በጥሬ ብር እና ከነ ቋሚ ንብረቷ 1,544,896 ብር ለመድረስ ችሏል። ይህ ካፒታል ከኦዲት ቁጥር በኃላ ሲሆን ተጨማሪ አምስት ኮምፒውተር ከነ ሙሉ አቃው፣ ፕሪንተር ፣2 ጠረጴዛ ፣ሁለት ሼልፍ በስጦታ መልክ ተበርከቶላቸዋል። የማህበራት አምስት አመራርና ዘጠኝ ንሁሳን ኮሚቴ የተሟላ መዛግብትና ሰነዶች በማዘጋጀት አባላቶቻቸው እንደሚያገለግሉ ተገንዝበናል።

ከምንም በላይ በዋናነት የአመት እቅዳችን በጠቅላላ ጉባኤ ለማፅደቅ ተግባር ላይ በማዋል የማህበሩ አመራሮች ከአባላቶቻቸው ጋር አስቀድመው በየሁለት ሳምንታት ስራ አፈፃፀማቸው  አባላቶቻቸው ለሚያነሱት ማናቸውም ጥያቄ መልስ  የሚሰጡበት እንዳላቸውና ጠቅላላ ጉባዬአቸውን በአመት አንዴ በማካሄድ ያለባቸው ችግሮች በጊዜው መፍትሄ እንደሚሰጡ  የገለፁት የበየና ማህበር ሊቀመንበር  ወ/ሮ ያየሽ ተክኤ ናቸው።

የጠቅላላ ጉባኤው ተሰብሳቢ በሚይዘው አጀንዳ ላይ ስፍራ ያገኘናት የሂሳብ ሰራተኛዋ ጥሩ አገልግሎት እንደምትሰጣቸው በማመስገን እንደ ችግር ያነሱት የኛ የሚሉት ፅህፈት ቤት አለመኖራቸው በመግለፅ ይህ በሂደት የሚፈታበት ሁኔታ እየተመቻቸ እንደሆነና ለጽህፈት ቤታቸው አገልግሎት የሚሆኑ እቃዎች እየተማላላቸው እንደሆነ የገለፁት የማህበሩ ም/ ኃላፊ ወ/ሮ ኬይስ ይህደጎ ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ  እንዳለ ማህበራ እንድታድግ ከተለያዩ ባለ ድርሻ አካላት ጋር በመተባበር እየሰራች እንደሆነ ገልፀዋል፡፡ ከሴቶቸ ጉዳይ ፅህፈት ቤት ከከተማዋ ከሌሎች ባለ ድርሻ አካላት  መንግስታዊ ካልሆኑ  ድርጅቶች  በመተባበር  እና በመተሳሰብ በተለይም በመንግስት  አቅም ሊሸፈኑ የሚችሉ ነገሮች ካሉ መንግስታዊ ድርጅቶች እንዲያገኙዋቸዉ  ያደርጋሉ፡፡ በዚህም በቅርቡ ከኒው ሚሊኒየም  ሆፕ ዲቨሎፕመንት  ኦርጋናይዜሽን የተለያዩ ተጨማሪ ዕቃዎቸ ሊያገኙ ችለዋል፡፡

በዚህ መሰረት አባላት ሆኑ አመራሮች በየጊዜው አዳዲስ  አባላት ያፈራሉ ፤ አንዲቆጥቡ እያበረታቱ የተበደሩትም ብር እነዲመልሱም ንቅናቄ ያካሂዳሉ፡፡ በዚህ ደግሞ አዳዲስ አባላት እያፈሩ  50 አቅደው  63 ጨምረው ይገኛ። በተመሳሳይ በዛ አመት 192,600 ብር እንዲቆጥቡ አቅደው ግን ካቀዱት በላይ 199,858 ብር የደረሱ እነዚህ አባላት በወር 30 ብር ይቆጥባሉ ከእነዚህ ደግሞ 250 አባላት ካለማቋረጥ በተከታታይ የሚቆጥቡ ናቸው፡፡ አዳዲስ አባላትም ከዚህ ተነስተው እያፈሩ የሚገኙት፡፡

ይህ በእንዲህ  እንዳለ የማህበራት አባላት እንደገለጹት በርከት ያሉ በቀበሌው የሚገኙ  እማወራዎች  መቆጠብ እንዳለባቸው  የማይቆጥቡበት  ሁኔታዎች እንዳሉ በምክክር መድረካቸው ላይ በጉልህ የተነሳ ችግር እንደሆነና ይህን ችግር እንደሚፈቱት  መግባባት ላይ ደርሰዋል፡፡

ከዛም በመቀጠል በየና ብድር ቁጠባ ሕ/ሰ/ማህበር 650 ሺ ብር ለማበደር አቅደው 482 ሺ ብር እንደ አበደሩና በዚህ የተገኘ ብድር  ለአባላቶቸ የተለያዩ የስራ ዘርፍ ላይ እንደ ሸመና ፤ ምግብ  ዝግጅት  ከፊት እና የተለያዩ  ችርቻሮ ንግድ እንዲሰሩ አድርጋለች፡፡

ወጣት ወርቁ ይሳቅ  እንደ ገለፀችው ቀደም ሲል  ምንም አይነት  የስራ ልምድ  ያልነበራት እና  ወዶ መስራት ይከብዳት ነበር፡፡ ነገር ግን  ይህ ፕሮግራም ከምን በኃላ ቤቶች ጉዳይ ቢሮ ሄጄ በመመዝገብ በግሌ ብድር ወስጄ መስራት ጀምሬ ያለሁ፡፡ በአሁን ሰዓት  ከማህበሬ እስከ 20,000 ብር ለመበደር ችያለሁ  ይህ ሁሉ  ደግሞ ከበየና ማህበር ባገኘሁት  ብድር ነው ስትል ማህበራን አመስግናለች፡፡

“ደሃ ከሆንክ  የናትህ ልጅም እያበድርህም ቢያበድርህም  ሊለወጥ የማይችል  ብር ነው፡፡ የሚሆነው እኔ ለረጅም ዓመታት  በጉልበት ስራ ተሰማርቼ ሰርቻለሁ ነገር ግን ዉሎ ከመግባት ያለፈ ምንም አይነት ለውጥ ለማግኘት አልቻልኩም ተደራጅታችሁ ኑኖአችሁን  ለውጡ የሚል ፐሮግራም ከኒው ሚሊኒየም ሆፕ ዲቨሎፕመንት ኦርጋናይዜሽን  አክሱም  ሴቶች ጉዳይ ፅፈት ቤት  ጥሪ ሲቀርብልኝ ባለ ማቅማማት ለመደራጀታችን  በየን ማህበር ብድር ወስጄ በመንቀሳቀሴ ሻይ ቡና ካፊቴሪያ፣ የወተት ላሞች ፣8 በጎች በመግዛት እያራባሁ እገኛለሁ::” ያሉት የማህበሩ ገንዘብ ያዥ  ወ/ሮ ሙሉ ሃያል ናቸው፡፡

በብድር መልክ አውጥተው ሊመልሱት ካሰቡት ብር 991,830 ብር 42, 132 ብር የተመለሰ ሆኖ ቀሪው 949,698 ብር የ448 ሴቶች  በቀጣይ  የሚመለስ ውዝፍ ዕዳ ነው፡፡

ሴቶች የተበደሩትን ብድር ለተፈለገበት አላማ እነዲያውሉት የሚከታተል አደረጃጀት ሌላው የማህበሩ ኃላፊነት ነው፡፡ ብድርና ቁጠባ ህ/ሰ/ማህበር በየና ከአባላቶቿ በተጨማሪ በከተማዋ ለሚገኙ  የሴቶች አደረጃጀት ብድር በመስጠት አድማሷን እያሰፋች  የምትገኝ አደረጃጀት ናት፡፡ እንበልና ለምሳሌ 10 ሴቶች ተደራጅተው ከብይን ብድር በመውሰድ  የንብ እርባታ  ስራ ላይ እንደ ተሰማሩና  55 ሺ ብር ተበድረው  የሽመና ስራ እየሰሩ የሚገኙ ሴቶችን ማህበራቸው በየና እንዳገዛቸው የመሰከሩት የማህበሩ አባላት ናቸው፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የተለያዩ  የልማት ከበየነ ብድር በመውሰድ ለአባላቶቻቸው  ተመልሰው ብድር በመስጠት 24 ሴቶች የብድሩ  ተጠቃሚ እንደሆኑና በጥሩ  ስራ እየተሰሩ እንደሚገኙና ብድራችው በጊዜው በመክፈል አሁን ቁጠባቸው ወደ 2,800 ሊደርስ እንደቻለ  የገለፁት የበየና ማህበሩ ፀኃፊ  የዕምበባ ልማት አደረጃጀት ሊቀመምበር ወ/ሮ ሂወት ወ/ስላሴ ናቸው፡፡

በተመሳሳይ ወ/ሮ አበባ አማረ የቅስነት ልማት አደረጃጀት  ሊቀመምበር ከበየነ ማህበር ብድር በመውሰድ ለአባላቶቻቸው ለማበደር በተለያየ የንግድ ዘርፍ ላይ እንዲሰሩ ለማድረግ ለራሳቸውና በቤተሰቦቻቸው የተሸለ ለውጥ እንዲመጣ አስችላለች በየነ ማህበር በማለት ይገልፃሉ፡፡

 

Leave a Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *